የቀለም አብዩት አለም አቀፍ ተሞክሮና ውጤቱ

የቀለም አብዩት አለም አቀፍ ተሞክሮና ውጤቱ

ቀለም አብዩት ከተካሄደባቸው አገሮች ርቀው ለሚገኙ ምዕራባዊያን የኒዩሊበራሊዝም የርዕዩተ አለም ልዕልና መፍጠር፣ ለኢንዱስትሪዎቻቸው በአንድ በኩል
ሰፊ ገበያ ማስገኘት፣ በሌላ በኩል ርካሽ ጥሬ እቃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ለእነዚህ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻቸው ስጋትና መጥፎ ምሳሌ የሚሆኑ መንግስታትን ማስወገድ መሆኑን አይተናል፡፡ በዚህም ከግሎባላይዜሽን ጋር ተያይዞ የኒዩሊበራሊዝም ሀይሎች ኮርፖሬት ተቋማት የቀለም አብዩት ሰለባ የሆኑ አገሮችን የተፈጥሮ ሀብት እንደልባቸው ለማግኘት ይጠቀሙበታል፡፡

በሌላ በኩል የቀለም አብዩት ሰለባ የሆኑ አገሮችስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለን ስንጠይቅ ጉዳዩ የተገላቢጦሽና የኒዩሊበራሊዝም ሀይሎችን ኢሰብዓዊነት ቁልጭ አድረጎ የሚያሳይ ሀላፊነት የጎደለው የማን አለብኝነት ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለአብነትም ሶሪያና የመንም እንደ አገር እየፈረሱ ሲሆን በቀለም አብዩት መልክ የተጀመረው አመጽና ሁከት ከዜጐቻቸው እጅ ወጥቶ በሌሎች እጅ በመግባት ወደ እርስ በእርስ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት / reginal powers የመሆን/ ውድድር ጦርነት ተቀይሮ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ከቀለም አብዩት ጋር በተያያዘ ምክንያት ዩክሬይን በዋናነት የፖሊሲ ነፃነቷን እንድታጣ ተደርጋለች፡፡ በተጨማሪም የመንግስት ህዝባዊ ተቀባይነት / public legitimacy / እየተዳከመ በመምጣቱ ራሷን ከዩክሬን ገንጥላ የሩሲያ ፌዴሬሽን አካል እንዳደረገችው ክራማያ የመገንጠል ጥያቄ አንስተው የሚዋጉ እንደ ዶኔክስ ያሉ ግዛቶችም እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡


በአጠቃላይ የቀለም አብዩት አለም አቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው የኒዩሊበራሊዝም ሀይሎች ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻቸውን ማዕከል አድርገው በአፍሪካ፣ በኤሲያና በላቲን አሜሪካ አገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት አሻንጉሊት መንግስታት እያቋቋሙ ወይም እያፈረሱ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ኢትዩጵያዊያን አገራችንን ከውጭ ጣልቃ ገቦች ጠብቀን፣ ውስጣዊ ችግሮቻችንን በመነጋገርና በመቻቻል እየፈታን በስውጣችን ልዩነትና መቃቃር ለመፍጠር የሚሽሎከሎኩ ተላላኪዎችን እየተቆጣጠርን ተጋላጭነታችንን በመቀነስ የቀለም አብዩትን በመከላከል ሰላማችንንና ልማታችንን መጠበቅና ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻልን መታየት የጀመረው እድገትና በህዝባችን የተፈጠረው የለውጥ ተስፋ ጨልሞ መጪው ሁኔታ በእርግጠኝነት የማንቆጣጠረውና የእጃችን የሌላ ብቻ ሳይሆን ህልውናችንም አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል የሚያጠራጥር ነገር የለውም፡፡

Comments