የኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ማብራርያ
1) መግብያ
የኢፌዴሪ መንግሥት የአገራችንን
ሕዝቦች የልማት፤ የፍትሕ፤ የዲሞክራሲና ሰላም ጥያቄን በተገቢው ሁኔታ ለመመለስ አስፈላጊ የለውጥ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። አገራችን የጀመረችውን ታላቅ የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል እና ጥልቀት ባለው መልኩ ሥር
እንዲሰድ ለማስቻል የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና በመፈተሽ ይህንን ለማሳካት በሚያስችል አደረጃጀት እንዲዋቀር ማድረግ
ተገቢ ነው። ይህም መንግሥት በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ያቀዳቸውን ግቦች
በተገቢው ሁኔታ ለማስፈጸም እንዲችል ያግዘዋል።

አሁን በሥራ ላይ ያለው የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፤ ሥልጣንና ተግባር
የሚወስነው አዋጅ በሥራ ላይ ከዋለ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ግዜ
ውስጥ ውስን ማሻሻያዎችን ብቻ አስተናግዷል።[1] የኢፌዴሪ መንግሥትትኩረት ሰጥቶ
ሊሰራቸው የሚገባቸው ቀዳሚ አጀንዳዎች የአስፈጻሚ አካላት በተቀናጀና ውጤትን ትኩረት ባደረገ መልኩ ተደራጅተው በከፍተኛ ትብብር ሊሰሯቸው እንደሚገባ ዕሙን ነው። እነዚህም ቀዳሚ
አጀንዳዎችሰፊ
የሥራ ዕድል ባጭር ጊዜ ውስጥ መፍጠር፣የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት
ማሳደግ፣የኢንዱስትሪ ልማትን በማፋጠን በአገራችን
ኢኮኖሚ ላይ መሠረታዊ መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፣ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደትን
ማጠናከር፣ የሕዝቦች ሰላምና መረጋጋት ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ፍትሃዊ
እና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማረጋገጥ የዜጎቻችንን ጥያቄዎች በበቂ ሁኔታ ማስተናገድ የሚሉት ናቸው።በዚህ
ረቂቅ አዋጅ የቀረበው አደረጃጀት እነዚህን ታላላቅ አጀንዳዎች ከግብ ለማድረስ በሚያስችል መልኩ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።የአስፈጻሚ
አደረጃጃት በወጪ ቆጣቢነት መርህ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን በሚያሳጥርናየውሳኔዎችን
መጓተትንና ከአንዱ ወደ ሌላው መገፋፋትን በሚያስወግድ ቅኝት ተዘጋጅቷል።

2) የአዋጁ አስፈላጊነት
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የአስፈጻሚ
አካላት በተቀናጀና ውጤታማነትን ትኩረት ባደረገ መልኩ ሊቃኙና ሊደራጁ ይገባል።የአስፈጻሚ
አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:

§ አገራችን የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠልና የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የሚያስችል አደረጃጀትን ለመከተል፤
§ የ2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በቀሪው ግዜ ያልተጠናቀቁሥራዎችን አካክሶ ለመፈጸም የሚያስችል
ዳግም የማደራጀት ሥራ መሥራት፤
ዳግም የማደራጀት ሥራ መሥራት፤
§ የአስፈጻሚ አካላትን ቁጥር በመቀነስ እና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆን በማድረግ በተቻለ መልኩ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና የተቀናጀ ካቢኔ ማቋቋምናየማስፈጸም አቅሙን ማጠናከር፤
§ ተደራራቢና ድግግሞሽ ሥልጣንና ተግባር የያዙ የመንግሥትተቋማትን መቀነስ ወይም ለሥራቸው ቅርብ ከሆነ ሌላ የመንግሥት
ተቋም ጋር እንዲዋሃዱ ማድረግ፤
ተቋም ጋር እንዲዋሃዱ ማድረግ፤
§ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ የሪፎርም ሥራ በጠቅላይ ሚኒስትር
ጽ/ቤት እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ነው። የሪፎርም ሥራው እስኪጠናቀቅ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተወዳዳሪ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ መወጣት እንዲችሉ፤ መንግስትም የባለቤትነት ሚናውና ተቆጣጣሪነቱ ባልተቀላቀለ
መልኩ የሚያስኬድ የመፍትሄ ሃሳብ ቀርቧል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጄንሲ ተቋቁሟል፤

·
ለሚኒስቴር መ/ቤቶች ተጠሪ ሊሆኑ የሚችሉ ተቋማት ካሁን
በፊት በስፋት በነበረው መልኩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ መሆናቸው ቀርቶ ለዘርፉ ቅርብ ሆኖ ለሚመለከተው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት
ሪፖርት እንዲያደርጉ፣ ሆኖም ከተልዕኮአቸው የተነሳ የግድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ መሆን የሚገባቸው
በዚሁ አግባብ እንዲደራጁ ተደርጓል።

3) ዋናዋናዓላማዎች
§ ሕገ-መንግስታዊ መብቶችን፣ ሰላምን፣ መረጋጋትንና የሕዝቦች ደህንነትን በዘላቂነት ማስጠበቅ፤
§ ፈጣንና ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ምቹ መደላድል መፍጠር፤
§ የኢንዱስትሪ ልማትን በማፋጠንና ኢንቨስትመንት በማስፋፋት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ማፋጠን፤
§ በአስፈጻሚ አካላት መካከል ጥብቅ ትስስርና ቅንጅታዊ አሰራርን ማስፈን፤
4) በአዋጁ የቀረቡ ዋናዋናማሻሻያዎች
የሚኒስቴር መ/ቤቶች ብዛት ቁጥር እንዲቀንስ የተደረገ ሲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት አሁን ካለው28ወደ 20ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ፤
§ አሁን በሥራ ላይ ያሉ አንዳንድ አስፈጻሚ ተቋማትና ተጠሪዎቻቸው እንደአስፈላጊነቱ በማዋሃድ ወይም በመነጠል አዲስ ተልዕኮ
ይዘው እንዲቀጥሉ ቀርበዋል፤
ይዘው እንዲቀጥሉ ቀርበዋል፤
§ አገራችን እየተገበረችው ያለውን ለውጥ በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችሉና በተለይም ለሰላም እና የሕግ የበላይነት ትኩረት
ሰጥቶ የሚሰራ “የሰላም ሚኒስቴር” የተቋቋመ ሲሆን ይህንንም ተልዕኮውን እንዲወጣ የሚያስችለውን ስልጣንና ተግባር እንዲይዝ ተደርጓል
፤

§ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ወይም ሌሎች አስፈጻሚ አካላት የሥራ ድግግሞሽን ለማስወገድ፣የተቀላጠፈ አገልግሎትን ለማቅረብ፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ ሲባል ተቀራራቢ ሥልጣንና
ተግባር ያላቸው ተቋማት እንዲፈርሱ፣ መዋሃድ የሚገባቸው እንዲዋሃዱ ተደርጓል፤ ስያሜያቸውም አጭርና ገላጭ እንዲሆን ለማድረግ
ጥረት ተደርጓል።

§ ከፍተኛ ካፒታል፣ የሰው ሃብትና የቴክኖሎጂ ግብዓት እንዲኖራቸው ተደርጎ የተደራጁና ለሚኒስቴር መ/ቤቶች
ተጠሪ ሆነው የቆዩ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን
በተመለከተ ከላይ እንደተቀመጠው በአዲስ ሁኔታ በኮርፖሬት ፋይናንስ ሕግ እንዲመሩ የሚያስችል ሥርዓትን
ለመከተል ይህንኑ አፈጻጸም የሚከታተል ኤጄንሲ ተቆቁሟል።

5) የአዋጁ አደረጃጀት
አዋጁ
አራትክፍሎች እና 37 አንቀጾች ያሉት ሲሆንክፍል አንድ ስር፣
አጭር ርዕስ እናትርጓሜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ይዟል።ክፍል ሁለትስለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ስለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር፣ ስለ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትና ስለ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የስብሰባ ስነ-ሥርዓት ይደነግጋል።በክፍል ሶስትስለሚኒስቴሮች መቋቋምና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹን ሥልጣንና ተግባር አንድ በአንድ ይዘረዝራል።በመጨረሻው በክፍል አራትልዩ
ልዩ ድንጋጌዎች የቀረቡ ሲሆን እነዚህም ስለ ተሻሩና ተፈፃሚነት ስለሌላቸው ሕጎች፣ ሃላፊነትን ስለማስተላለፍ እንዲሁም አዋጁ ስለሚጸናበት ጊዜ ቀርቧል።

6) የአዋጁዝርዝርይዘት
6.1 ስለሚኒስቴሮችመቋቋም
በቀረበው አዲስ መዋቅር እና አደረጃጀት 19 ሚኒስቴሮች ተቋቁመዋል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-
2. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር
4. የገንዘብሚኒስቴር
5. የጠቅላይ አቃቤ ሕግ
6. የግብርና ሚኒስቴር
7. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
10. የትራንስፖርት ሚኒስቴር
11. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
12. የውሃ ፤መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
13. የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
14. የትምህርት ሚኒስቴር
15. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶች፤ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር
18. የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
19. የባህል እናቱሪዝም ሚኒስቴር
6.2 የሚኒስትሮችምክርቤትአባላት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከላይ በቁ. 6.1የተዘረዘሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የምክር ቤት አባል የሚሆኑ
ሲሆን ሌሎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ እንደሚኖሩ በረቂቁ ተግልጿል፡፡

6.3 በረቂቅ አዋጁ ስለተቋቋሙ
አስፈጻሚ አካላት በሚመለከት
1.
የሰላም ሚኒስቴር
የሰላም ሚኒስቴር
በአገራችን የተጀመረውን
ለውጥና እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተማማኝና ዘለቄታዊ እንዲሆን ለማስቻል እና አበረታች ጅማሮዎችን ከግብ ለማድረስ የአገራችንን
እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም ማስጠበቅ የሚችል ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል። ለዚህም ትኩረቱ ሰላምን ማስፈንና የሕግ የበላይነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ የሚችል መንግሥታዊ መዋቅር መዘርጋት ግድ ይላል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዊነት ዕሳቤ በአገራችን ሕዝቦች ዘንድ ብሔር፣ ሐይማኖት፣ ቋንቋ እና ሌሎች ልዩነቶች ሳይገድቡት እንዲጠነክር ለማድረግ ስትራቴጂዎችን ነድፎ፣ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ ኃላፊነት የተሰጠው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ያስፈልጋል።

ይህ የሰላም ሚኒስቴር በአገር ውስጥም ሆነ በቀጠናችንየሕግ
የበላይነት እንዲሰፍንና ሰላም እንዲስፋፋ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። የሕግ የበላይነት መርህ በመንግሥት ሥልጣን፣ አሰራር እና ተጠያቂነት
አንፃር ጥብቅ ገደቦችን የሚመሰርተውን ያህል፣ ግለሰቦችም የወጡ
ህጎችን አክብረው እንዲኖሩ፤ ልዩነትም ሆነ ቅሬታ ሲኖራቸውም የተቀመጡ ሕጋዊ ስነ-ስርአቶችን ብቻ በመከተል መብቶቻቸውንና
ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ ያስገድዳል። የሰላም ሚኒስቴርም
ከሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘላቂ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፣ በሕግ የበላይነት እና በሕዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ
የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

ከስሙ ጀምሮ የተሰጠው ተልዕኮ ግልጽ ሆኖ በተለይም በማህበረሳባችን ለዘመናት የቆየውን አብሮነት፤ መቻቻል እና የአንድነት መንፈስ
በተጠናከረ መልኩ እንዲጎለብት በንቃት ይሰራል። በክልሎች መካከል ያለውን መስተጋብር እና ግንኙነት እንዲጠናከር ያግዛል። ከዚህ በተጨማሪ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎችእንደዚሁም በክልሎች መካከል በመግባባትና በአጋርነት ላይ የተመሠረተ መልካም ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር በማድረግ የፌዴራል ስርዓቱ እንዲጠናከር
የግንኙነት ማዕከል በመሆን ያገለግላል።

በአገራችን እየተተገበረ
ያለውን የተጠናከረ የዲሞክራታይዜሽን ሂደት በዘለቄታዊ መልኩ ለማስቀጠል የመከባበር፣ የመቻቻል እና አብሮ የመኖር ኢትዮጵያዊነት ባህል በሕብረተሰቡ መካከል ለማስረጽ የነበሩንን በጎ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና የሞራል ዕሴቶች በፍቅር፣ በመተባበርና በአንድነት መንፈስ ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ለማስተባበር፤ በማህበረሰቡ
ዘንድ ለረጅም ዘመናት በሕብረተሰባችን ዘንድ ዳብሮ የቆየውን ሶሻል ካፒታል ለፖለቲካዊ መቻቻል ለማህበራዊ ኑሮ መጸልጸጊያና ከአቅም
በላይ በሆነ መንገድ የሚከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ማሕብረሰብ-አቀፍ መፍትሔ ለመስጠት እንዲቻል ይህ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአዲስ
ዕይታ እና ዕሳቤ እንዲደራጅ ተደርጓል።

የሕዝቡ ሰላም መጠበቁን ለማረጋገጥ አግባብ
ካላቸው የፌደራልና የክልል መንግሥት አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከል የሰላምና የመከባበር ባህል እንዲዳብር የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልቶችን ይቀይሳል ፤ ከሚመለከታቸው የባህልና የኃይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት በመሥራት የሰላም ማስፋፋት
ሥራ ይሠራል፤በተለያዩ ኃይማኖቶችና እምነቶች ተከታዮች፣ እንዲሁም በተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል ሰላምና መከባበር
እንዲሰፍን ለማድረግ አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት
አገልግሎት ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ፤ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ መዕከል፣ የፌደራል ፖሊስ
፣የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፤ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን፣ ብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራን (የስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት ኤጀንሲን ሥራ አዋህዶ) እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ዓለም አቀፍ የሰላምና የልማት ኢንስቲቲዩት ሥራን በበላይነት ይመራል። ይህ አደረጃጀትም
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሕገመንግስታዊ የመዘዋወር መብቱ በሁሉም ቦታ ተገቢውን ሕጋዊ ጥበቃ እንዲያገኝ ከማስቻሉም ባለፈ የዜግነት
ክብር ጉዳይ በመንግሥትና በሕብረተሰቡ ዘንድ ተገቢውን ሥፍራ እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

ከዚህም በተጨማሪ በፌደራልና የክልል መንግሥታት መካከል ያለውን ግንኙነት
ለመምራት፤ በአገራችን አርብቶ
አደር ክልሎች ያለውን ከልማት በእኩል ተጠቃሚነት የመሆን ጥያቄ እንዲሁም ከግጦሽ መሬትና ከውሃ ዕጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታትመንግስታዊ አካላትን አስተባብሮ ምላሽ መስጠትእንዲቻል
ከዚህ ቀደም በፌዴራልና የአርብቶ አደር ጉዳዮችና ልማት ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩ ተግባርና ኃላፊነቶች ወደ ሰላም
ሚኒስቴር እንዲተላለፉ ሆነዋል።

2.
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር
የአገር መከላከያ
ሚኒስቴር አሁን የያዘውን ሥልጣንና ተግባር ይዞ ይቀጥላል። በመሆኑም በዋናነትየአገሪቱን የግዛት ሉዓላዊነት ያስከብራል፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአደጋና ጥቃት
ይከላከላል፤ አገር መከላከልን በሚመለከት አግባብ ያላቸውን የፌደራልና የክልል አካላት በመተባበር ይሠራል፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፤ የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽዖ ያካተተ መሆኑን
ያረጋግጣል፤ ተግባሩን ለሕገ-መንግሥቱ ተገዢ እና ከፖለቲካ ድርጅት ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ማከናወኑን ያረጋግጣል፡፡

3.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቀደም ብሎ ሲሰራበት የነበረውን ሥልጣንና ተግባራት ይዞ የሚቀጥል ሲሆንየኢትዮጵያን ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር፣ በጋራ
ጥቅምና እኩልነት ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ይቀርጻል፣ በሥራ ላይ ያውላል፡፡ አገሪቱ ባላት
የውጭ ግንኙነት ጥቅሟና መብቷ እንዲጠበቅና በሌሎች መንግሥታት እንዲከበር ያደርጋል፤ አገሪቱ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያላት መልካም
ጉርብትና እንዲጠናከር ያደርጋል እና ሌሎች በዚህ አዋጅ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባር ይፈጽማል፡፡

በቅርቡ የተቋቋመው
የዲያስፓራ ኤጄንሲ ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን የዲያስፓራን ተሳትፎ ለማጎልበት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

4.
የገንዘብሚኒስቴር
የገንዘብሚኒስቴር
የገንዘብሚኒስቴር ቀደም ብሎ ለገንዝብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ተሰጥቶ የነበረውንሥልጣንና ተግባራት ይዞ እንዲቀጥል ተደርጓል።
ሌላው ጉዳይ የሚመለከተው የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ሲሆን ድርጅቶቹ በአንድ በኩል እንደአትራፊ ድርጅት፣ በሌላ በኩል ደግሞ
እንደልማት ተቋም እንዲተዳደሩ የሚቃረኑ ሁለት አቅጣጫዎች መቀመጣቸው ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፤ የልማትና የትርፍ ማግኘት
ሚናዎች ሊለዩ ይገባል፤ የድርጅቶቹ የቦርድ አወቃቀር ተቋማቱን ትርፋማ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ሊቃኝ ይገባል፤የመንግሥት ቁልፍ ሚና
የሆነው ሬጉሌሽን (ቁጥጥር) በልማት ድርጅቶች ላይ ካለው የባለቤትነት ሚና ተለይቶ ሊታይ ይገባል፤ ከዚህ በተጨማሪ አላማቸው በአመዛኙ የንግድ የሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ይሆናል፡፡ በመሆኑም
ዋና አላማቸው ወደ ንግድና ትርፍ ያመዘኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በተመለከተ የመንግስት የባለቤትነትናየተቆጣጣሪነት
ሚና እንዳይቀላቀል፤ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጄንሲ ተጠሪነቱ ለገንዘብ ሚኒስቴር ሆኖ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የገንዘብ ሚኒስቴር የፕራቬታይዜሽን ሂደቱን በጥንቃቄ በመምራት ቁልፍ በሆኑ ድርጅቶች ላይ መንግሥት ዋና ባለቤትነቱን ሳይለቅ የሌሎቹን ደግሞ ሙሉ
በሙሉ ፕራይቬታይዝ እስከማድረግ ያሉ አማራጮችን ይመራል፡፡

5.
የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
የጠቅላይ ዓቃቤ
ሕግ አሁን በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ይዞ የሚቀጥል ሲሆን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መባሉ ቀርቶ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
ተብሎ ተሰይሟል። በማቋቋሚያ አዋጁ ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባር በተጨማሪ የወንጀል ምርመራ የሥራ ሂደትን
በሕግ ባለሙያዎች በታገዘ፤ ወጥነት ባለው መልኩና የተጠርጣሪዎች ሕገ-መንግስታዊ መብቶች ሳይጣሱ ምርመራ መካሄዱን ለመቆጣጠር እንዲያመች
የጠቅላይ አቃቤ ጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ሥራቸው ከሚጠይቀው የሕግ ሙያ ዕውቀት አንጻር የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ እናየኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲሆን ቀርቧል።
6.
የግብርና ሚኒስቴር
የግብርና ሚኒስቴር
የግብርናና የእንስሳት
ሃብት ሚኒስቴር ስሙ ላይ ማስተካከያ ተደርጎበት የግብርና ሚነስቴር ሆኖ የነበረውን ሥልጣንና ተግባር ይዞ፣እንዲቀጥል ቀርቧል።የእንስሳት ሃብት ልማትም ቢሆን
በግብርና ዘርፍ የሚወድቅ ከመሆኑ አንጻር ስሙ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኗል። ስለሆነም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እርሻን፣የተፈጥሮ ሀብትን፣ እና የእንስሳት ሃብትን፤ ዓሳ ሀብትን የተመለከቱ ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለግብርና ሚኒስቴር ተሰጥቷል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸርና ግብርና ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ሰሰራ የነበረውን የታላላቅ የግብርና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋትና የመደገፍ ተግባር በግብርና
ሚኒስቴር የሚሰራ ይሆናል፡፡
ሚኒስቴር የሚሰራ ይሆናል፡፡
7.
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
የንግድ ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ
ሚኒስቴር
በአንድ
የተዋሃዱ ሲሆን ይህም በአንድ ሚኒስቴር ስር ንግድና ኢንዱስትሪን በማጣጣም የማስፋፋት ሥራ ለመሥራት ያግዛል። የአንድ አገር የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ
መሳሪያ ከሆኑት መካከል ወጥነት ያለው የንግድ ፖሊሲና የገቢያ ዕድል ማመቻቸት ትልቅ ድርሻ አለው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚመረተው ምርት የወጪ
ንግድ የሚስፋፋበትን ዕድል በመፍጠርና የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ከውጭ በሚገቡ ምርቶች አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የተቀናጀ ፖሊሲ
ለመተግበር ትልቅ አቅምን ይፈጥራል።መንግሥት የንግድና ኢንዱስትሪ ልማትን በአንድ የፖሊሲ ማዕቀፍ ማስፈጸም
ያለበት መሆኑን በማመልከት ወጥነት ባለው የፖሊሲ ሰነድ የሚመራ ሲሆን፤ የንግድና የኢንዱስትሪ ልማትን በተሻሻሉ ሕጎች፣ መመሪያዎችና አሰራሮች አጠናክሮ ለማስቀጠል
አሁን ያለውን አስፈጻሚ አካል አደረጃጀት እንዲቀየር ቀርቧል።

ከዚህ በተጨማሪ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን
አቅም በመገንባት እና ለዚህም አስፈላጊውን የፖሊሲ ድጋፍ በመንደፍ ይሰራል። የግል ዘርፍ ዕድገት ለመጨመር በተናበበ መልኩ
የሚወጡ የንግድና ኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞችን ይተገብራል። በመሆኑም በቀጣይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
መ/ቤቶችን አዋህዶ አንድ የመንግሥት አስፈጻሚ ተቋም በማደራጀት ተመጋጋቢነት ያላቸውን ተግባራት ውጤትን መሰረት አድርጎ መቃኘት፤ በተናጠል ሲሰሩ የነበራቸውን ልምድ እያደገ
ከመጣው የኢኮኖሚ ሁኔታና የልማት ፍላጎት ጋር ማዋደድ፤ ለውጭ ንግድ መጠናከር ሊሰሩ የሚገቡ ሥራዎችን በስፋት በመሥራት የአገራችንን
የውጭ ንግድ የማስፋፋት ሥራ መሥራት እንዲችል ያደርገዋል። የስራ ድርርቦሽን ለማስወገድ የውጭ ባለሐብቶችን
በተመለከተ የሚደረግ የምልመላ፤ የድጋፍና የቁጥጥር ስራ በዋናነት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሚሰራ ይሆናል፡፡

አሁን የሚታየውን የሥራ ድግግሞሽንና በፈጻሚዎችና በተገልጋዮች
በኩል የግልጽነት ችግርን ለማስወገድ ብሎም ከኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተለይ
በቀድሞው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥር የሚገኙ ኢንስቲትዩቶች የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን የተሟላ ድጋፍ በመስጠት ከምርት እስከ ግብይት፤
ኤክስፖርትን ጨምሮ እንዲደግፉ ቀርቧል፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመጣመር
የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያላቸው ሚና እንዲያድግ ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአገራችንን የውጭ ንግድ በከፍተኛ
ሁኔታ ለማሳደግ አስፈላጊውን የውጭ ንግድ የማስፋፊያ ስራ የሚሰራ ይሆናል። ቀደም ብለው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር የነበሩት
የተለያዩ የልማት ኢንስቲትዩቶች በቀጣይ ሲመሰረቱ የተሰጣቸውን ዓላማና ተግባር ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ከፍተኛ
ክትትልና ድጋፍ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይጠበቃል።እነዚህ ኢኒስቲቲዩቶች በአመዛኙ የኢንዱስትሪ ባለሀብቱ የሚያጋጥሙትን አስተዳደራዊ
ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የማሳለጥ ሥራ ላይ በስፋት እየሰሩ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ የፋሲሊቴሽን ሥራ በበለጠ ግን የሚጠበቅባቸው
በማቋቋሚያ ደንቦቻቸው ላይ እንደተቀመጠው የምርምር ተቋም በመሆን የአገራችን ባለሀብቶች
ዘመን የደረሰበት ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም የሚያስችለው በጥናት የታገዘ ድጋፍ እና ክትትል እንዲያቀርቡ ነው።ዓላማቸውም ልማትንና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ
እንዲሆኑና ፈጣን ልማት እንዲያስመዘግቡ ማብቃት ነው።ይህንን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት አድርጎ
የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማትን እንዲመራ ይጠበቃል፡፡

8.
የገቢዎች ሚኒስቴር
የገቢዎች ሚኒስቴር
የገቢዎችና ጉምሩክ
ባለስልጣን ከፍተኛ ስፋት ያለው ስራ የሚሰራ ሲሆን የአገር ውስጥ ገቢንም ሆነ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰበስበው ይኸው ተቋም ነው፡፡
ይሁንና የግብር አሰባሰብ አፈጻጸም መንግስት ባቀደው ልክ እና እያደገ ካለው ኢኮኖሚ የተጠጣመ ገቢ እየሰበሰበ እንዳልሆነ እሙን
ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጉምሩክ አገልግሎት ቀረጥ በመሰብሰብ ከሚገኘው ገቢ በእጅጉ በበለጠ ቀልጣፋ፤ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ
፤ ወጪ ቆጣቢ እንዲሆን ማስቻል ለወጪ ንግዳችንም ሆነ ለጠቅላላው አለም አቀፍ ንግድ አይተኬ ሚና ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ባለስልጣን
መስሪያ ቤቱ ያለው አደረጃጃት ይህንን በተገቢው ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችል አይደለም፡፡ የሌሎች አገራትም ልምድ የሚያሳየው የአገር
ውስጥ ገቢና የጉምሩክ ስራው ተነጥሎ መያዝ እንዳለበት ነው፡፡ ስለሆነም የጉምሩክ ጉዳይን የተመለከተ ስራ የሚመራ የጉምሩክ ኮሚሽን
ተቋቁሟል፡፡

ይህ የቀረበው አዲስ
አደረጃጀት የጉምሩክ ተቋሙ ትኩረቱን ቀረጥ ከመሰብሰብ ባለፈ የንግድ ማሳለጥ ላይ እንዲያተኩር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

9.
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ተብሎ የሚጠራ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት
ተቋቁሟል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዋናነት ያለው ሥልጣንና ተግባር የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ መሰረት ያደረገ የፈጠራ
ስራ እንዲስፋፋና የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ በማጸደቅ ተግባራዊ እንዲደረግ አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት አፈጻጸሙን
መከታተል ነው። በተመሳሳይ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
ልማት ፖሊሲን በብቃት እንዲያስፈጽም የተቋቋመ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነው። እነዚህ ዋና ዓላማቸው ተዛማጅና የማይነጣጠሉ ተግባራትና ሥልጣናት ያሏቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በአንድ ማዋሃድ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። ይህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍን በማጠናከርና ወጥነት ያለው ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ በማስፈጸም ለኢኮኖሚ ልማት ያለውን
ሚና በተገቢ ሁኔታ እንዲወጣ አዲስ አቅምን ይፈጥራል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር
አሁን በስራ ላይ ያለውን ሥልጣንና ተግባር ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ አልተደረገበትም።

11.
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
የከተማ ልማት ተግባር ሁለገብ የልማት ሥራን የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም የንግድ፣ የመሠረተ ልማት፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎችን ያጠቃለለ ሆኖ
የእነዚህን ተግባራት ቅንጅትና ትስስር የሚጠይቅ ዘርፍ ነው። በተመሳሳይ መልኩ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
የተለያዩ ሃብቶችን ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ ወደሆኑ የግንባታ ውጤቶች የሚለውጡ
እና ዕሴት የሚፈጥር ዘርፍ ነው። በመሆኑም አገራችን እያስመዘገበች ያለውን
ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት መገለጫ የሆኑትን ዓበይት ተግባራትን የያዙ እነዚህ ዘርፎች ከዚህ
በፊት በተናጠል ሲያከናውኑት የነበሩትን ተግባራት በማሰባሰብና ካላቸው ተዛማጅ ኃላፊነት አንጻር በቁጥጥርና አስተዳደራዊ ጉዳዮች
የሚታየውን የቅንጅት መላላት፤ በመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታየውን የጥራት መጓደልና በዘርፉ የሚታዩትን ህገ-ወጥ መበልጸግ በተቀናጀ
ኃይል ለመታገል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚያሰችል አግባብ ማደረጃት ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።

ስለሆነም የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር
በአንድ ላይ ተዋህደው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሚል ተደራጅተዋል።

በአገራችን ከግንባታ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የቁጥጥር
ክፍተት በዚሀም የተነሳ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሃብት ብክነት በተገቢው ሁኔታ ለመቆጣጠር እንዲያመች ተጠሪነቱ ለከተማ
ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሆነ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

12. የውሃ፤ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
አገራችን ካሏት በርካታየተፈጥሮ ሃብቶች መካከል በተገቢው ሁኔታ ጥቅም ላይ ማዋል
ያልተቻለ አንድ ሃብት ነው፤ አገራችንን የውሃ ማማ ያስባሏት ብዙ ወንዞች እና ከረሰምድር የውሃ
ሀብት አለን። ሆኖም ግን ዛሬም ድርስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን
የንፁህ ውሃ መጠጥ አቅርቦት እንኳ የሌላቸው መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የአገራችንን ግብርና አሁን ካለበት ባህላዊ የአስተራረስ
ዘዴ ወጥቶ በተለይም የዝናብ ውሃን ብቻ በመጠበቅ የሚደረግ ምርት ምንም ያህል ግብርናውን ሊያሳድገውም ሆነ ሊያዘምነው አልቻለም። ስለሆነም የመስኖ ግድቦችን በመጠቀምና የከርሰ
ምድር ውሃን በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎችን ማልማት ግዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው። በመሆኑም ይህንን የመስኖ ልማትን የሚያፋጥን
ሥራ ለመሥራት እንዲቻል የመስኖ ልማት ኮሚሽን ተቋቁሞ ለዚህ
ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተጠሪ እንዲሆን ይደረጋል።በተመሳሳይ ትኩረቱን የውሃ ልማት ላይ ያደረገ
የውሃ ልማት ኮሚሽን በዚህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስር ይቋቋማል፡፡
የነዚህ ኮሚሽኖች ዝርዝር ስልጣንና ተግባር በደንብ የሚወስን ይሆናል፡፡

የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለማሳደግና ስርጭቱን ለማስፋፋት
ከዉሃ ኃይል ፣ ከንፋስ ኃይል እና ከሌሎች አማራጭ ታዳሽ ኃይል አሌክትሪክ የማመንጨት ስራ በዚሁ ሚኒስቴር ስር ይሆናል

የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማስቀጠልና መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳለጥ የተፈጥሮ
ሃብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል የግብርና ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ፤ በአመት ከአንድ ግዜ በላይ በማምረት በምግብ
እህል ራስን የመቻል ጥረት ማገዝ ተገቢ በመሆኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሥራዎችን አንድ ላይ አቀናጅቶ የሚያስተባብርና የሚተገብር የውሃና፣
መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይሆናል።በተጨማሪ የተፋሰስ
ልማትና ጥበቃን ለማጠናከርና በተቀናጀ ሁኔታ ለማስኬድ በሥሩ ያሉት የአባይ ተፋሰስ ባለሥልጣን፣ የአዋሽ ተፋሰስ ባለሥልጣን እና፣ የስምጥ
ሸለቆ ተፋሰስ ባለሥልጣን በአንድላይ “የተፋሰስ ባለሥልጣን” ሆነው እንዲቀጥሉ ቀርቧል።

የማዕድንና ነዳጅ
ሚኒስቴር በስሙ ላይ ብቻ ማስተካከያ ተደርጎበት የያዘውን ስልጣንና ተግባር ይዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የማዕድን ዘርፍ
ለአገራችን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት እና ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር አስተዋጽዖ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ማድረግ ተገቢ
ነው። አገራችን ካላት ዕምቅ የማዕድን ሃብት አንጻር ብዙም ተጠቃሚ እንዳልሆነች
የሚታወቅ ነው። ለዚህም የመረጃ ክፍተት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፣ በአምራቾች አካባቢ
የግዥ ማዕከላት
አለመስፋፋት፣ የማምረቻ መሳሪያዎች አቅርቦት ዕጥረት፣ የመሠረተ ልማት አለመሟላት የሚሉት ይገኝበታል።

የማዕድን ዘርፉ በነዳጅ ዘይት እና በጋዝ ምርት ትኩረት በመስጠት ለአገራችን
ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጾ እንዲኖረው ማስቻል ተገቢ ነው፡፡
ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጾ እንዲኖረው ማስቻል ተገቢ ነው፡፡
14. የትምህርት ሚኒስቴር
መንግሥትባለፉት
ሁለት አስርት አመታት ትምህርትን በማስፋፋት እና ተደራሽነቱን በመጨመር ትልቅ እመርታ ቢያሳይም የትምህርት ጥራት ግን በእጅጉ እየተዳከመ
እንደመጣ ሁሉም የሚገነዘበው ነው።ይህንን የትምህርት ጥራት ጉድለት በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል እንዲቻል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል። ለዚህም የትምህርት ሚኒስቴር ትኩረቱን ጠቅላላ ትምህርት ላይ አድርጎ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ክፍተቶችን
በመለየት እንዲሰራ በማሰብ የከፍተኛ ትምህርትን የተመለከተው ዘርፍ አዲስ በተፈጠረው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲመራ
ተደርጓል።

15. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት
ሚኒስቴር
ሚኒስቴር
በአገራችን እየተስፋፋ
ያለውን የከፍተኛ ትምህርት በተጠናከረ መልኩ ድጋፍ አግኝቶ ጥራትን በአማከለ መልኩ የትምህርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የከፍተኛ
ትምህርት ሚኒስቴር ማቋቋም አስፈላጊ ሆኗል። ይህ ሚኒስቴር በዋናኛነት
የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በቅርበት በመከታተል አሁን በእጅጉ እየታየ ያለውን የትምህርት ጥራት በማሳደግ ተመራቂዎች
በየትኛውም የዓለም ክፍል ተወዳድረው መቀጠር የሚችሉበትን ዕውቀትና ክህሎትን ጨብጠው እንዲወጡ ያደርጋል።ከዚህ በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ በበላይነት ይመራል፤የከፍተኛ ትምህርት ከአገሪቱ
አጠቃላይ የልማት ፖሊሲና ከዘርፎች ዕድገት ጋር አብሮ ለማስኬድ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ጥናት ያካሄዳል፣ በሥራ ላይ ያውላል፤ የከፍተኛ
ትምህርት የሥርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊያሟሉ የሚገባቸውን ደረጃ ያወጣል፤ የመንግሥት የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማትን ያስተዳድራል፣ ይከታተላል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት የሚያደርጉትን የምርምር ስራ ሳይንስ ላይ ትኩረት በማድረግ ተገቢውን ጥናት እያደረጉ ለአገራችን ልማት ተገቢውን አስተዋጾ
እንዲያደርጉ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡ ለዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመሠረታዊ የሳይንስ ጥናትና ምርምር የጎለበቱ እንዲሆኑ የሚያስችል
ስልት ይነድፋል፣ ይተገብራል፤ የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ውጤቶች በሥራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡

በአገራችን ያሉ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትተጠሪነታቸው ለዚሁ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይሆናል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትተጠሪነታቸው ለዚሁ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ይሆናል።
16. የጤና ሚኒስቴር
በጤና ሚኒስቴር
ሥልጣንና ተግባራት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ያልተደረገበት ሲሆን በስሙ ላይ ብቻ “ጥበቃ” የሚለው እንዲወጣ ተደርጓል።

17. የሴቶች፤ ህጻናትና ወጣቶች
ጉዳይ ሚኒስቴር
ጉዳይ ሚኒስቴር
ሴቶች ለዘመናት የደረሰባቸውን ባህላዊ እና ታሪካዊ ተጽዕኖ በመሻር በእኩልነት ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ተሳትፏቸውን በተጠናከረ
ሁኔታ ለማስፋት እንዲቻል በጥናት ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎችን የሚቀርጽ እና የሚተገብር፣ ለሴቶች መብትና ጥቅሞች መከበር ግንዛቤና
ንቅናቄ የሚፈጥር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነው። በተጨማሪም ይህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቤተሰብን መሰረት
አድርጎ የሕጻናት ደህንነትና ጥቅምን ቀዳሚ ባደረገ መልኩ ይሰራል፤ አገራችን እውቅና የሰጠቻቸውና በሕገ-መንግስቱ
የተካተቱ የሕጻናት መብቶች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸውን ይከታተላል።ቤተሰብ የማህበረሰቡ መሰረት እንደመሆኑ ለዘመናት
ያቆየነውን ቤተሰብ ተኮር ዕሴቶች በመጠበቅና በማጠናከር ለሴቶች፤ ህጻናትና ወጣቶች መብትና ጥቅም ተግቶ ይሰራል፡፡

18. የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳዮች
ሚኒስቴር
ሚኒስቴር
የሰራተኛና ማህበራዊ
ጉዳዮች ሚኒስቴር አሁን የያዘውን ስልጣንና ተግባር ይዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ጉዳዮች ሚኒስቴር አሁን የያዘውን ስልጣንና ተግባር ይዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
19. የባህል እናቱሪዝም ሚኒስቴር
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አሁን ከተሰጠው ሥልጣንና ተግባራት በተጨማሪ
ስፖርትን የተመለከቱ ሥልጣንና ተግባራት ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በመጨመር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴር ሆኖ እንዲቋቋም
ተደርጓል። ይህም ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ ስፖርት ከባህልና ቱሪዝም ጋር ያለውን
ትልቅ ቁርኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።በዚህ መሠረት
በሥሩ የሚቋቋመው የወጣቶችና
ስፖርት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያሏቸውን ዕምቅ ባህላዊ የስፖርት ሃብቶች ከማሳደግ እና
ከማስተዋወቅ ባለፈ ይህንን ሃብት ለቱሪዝም መስህብነት የሚውልበትን ሁኔታ በተጠና መልኩ ለመሥራት
ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል። ይህ አደረጃጀት በዘመናዊ ስፖርት ተሳትፎም
የአንድ አገር ባህል የሚንጸባረቅበት ከመሆኑም ባለፈ ለስፖርት ታዳሚው አገርን በማስተዋወቅ የቱሪስት ፍሰትን በመጨመር ጉልህ ድርሻ
ይኖረዋል። በተጨማሪም በአገር ውስጥ የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች በሕዝቦች መካከል መቀራረብንና
የባህል ትስስርን ለማሳደግም ያግዛል።

ወጣቶችን በተመለከተ
ለወጣቶችና
ስፖርት ሚኒስቴር የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት በዚህ ሚኒስቴር ሥር እንዲካተቱ
ቀርቧል።
ስለሆነም
የወጣቶችን መብትና ጥቅሞችን ማስከበር፤ ወጣቶችን በሃገሪቱ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት
እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ዕድሎች ማረጋገጥ የመሳሰሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይወጣል። ስለሆነም መንግሥት ስፋት ባለው የፖሊሲ ማዕቀፍ
ተደግፎ በቀጣዮቹ ዓመታት የወጣቶችን ጉዳይ አዋህዶ የሚሰራና በሌሎች
ተቋማትም የወጣቶች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን
(mainstreaming) የሚያረጋግጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነው፡፡

7)ሌሎችአስፈጻሚአካላትና ተጠሪ መስሪያ ቤቶች
ከላይ የተዘረዘሩት
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ተቋማት ሥልጣንና ተግባራቸው እንደሚከተለው ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ፤ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ እንዲሆኑ ተደርጓል።

አዲስ የተቋቋሙና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ መስሪያ ቤቶች
አዲስ የተቋቋሙና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ መስሪያ ቤቶች
1.
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ ፈርሶ ስልጣንና
ተግባሩ ፤ መብቱንና ግዴታው በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተላልፏል፡፡ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ
ሚኒስትሩ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ይህም ኮሚሽኑ የተጣለበትን ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራ በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ተገቢውን
አቅጣጫ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያገኝ ያስችለዋል ፡፡ የሚከተሉት ተቋማትም ተጠሪነታቸው ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይሆናል፤

o
የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
o
መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ
መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ
o
የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት
የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት
o
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት
o
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
2.
የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን
የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን
መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት አንዱና ዋናው ትልቅ ጉዳይ የስራ
ዕድል ፈጠራ ይሆናል፡፡ ለዜጎች በቂ የስራ ዕድል መፍጠር ከአገራችን የብሔራዊ ደህንነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑ የማያጠያይቅ
ነው፡፡ ስለሆነም ሌሎች በዚህ ጉዳይ ከሚሰሩ የመንግስትም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማስተባበር ይህ ኮሚሽን ለስራ ዕድል
መፈጠር የሚያስፈልጉ ምቹ ሁኔታዎችን መፈጠራቸውን ያረጋግጣል፡፡ ይህ ኮሚሽን ተጠሩነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን ዝርዝር ስልጣንና
ተግባሩ በደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡

የአካባቢ ፤ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ
ኮሚሽን
የአካባቢ ፤ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ
ኮሚሽን
የአካባቢ ፤ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በዚህ አዋጅ የተቋቋመ ሲሆን
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የአካባቢ፤ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ተሰጥቶት የነበረውን ስልጣንና ተግባር ይዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገ ሲሆን ይህም በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉት የአካባቢ ደህንነት ዓላማዎችና በአገሪቱ
የአካባቢ ፖሊሲ የተመለከቱት መሰረታዊ መርሆዎች ከግብ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን በቅርበት ለመከታታል
ያግዛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ክትትል ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴኢኮኖሚን በየዘርፉና በየክልሉ
ለመገንቢያየሚውል ሃብት የሚያስገኙ ተግባራትዝግጅትን ያስተባብራል፤ የአቅም ግንባታድጋፍንና የምክር አገልግሎትን ይሰጣል፡፡

ቱሪዝምኢትዮጵያ
ቱሪዝምኢትዮጵያ
ቱሪዝም ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ሲሰራ የነበረው ስራ
የሚመራ ሲሆን በዋናነት ገቢውን ከተለያዩ ምንጮች በማስገኘት የአገራችንን የቱሪዝም ዕድገት ለማፋጠን የሚሰራ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት
ከመንግስት በጀት ውጭ ሆኖ እረሱ በሚያሰባስበው የተለያዩ ገቢዎች የሚተዳደር ይሆናል፡፡ ስለሆነም የቱሪዝም ፈንድ በማቋቋም ያስተዳድራል፡፡

5. የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን ጽ/ቤቱ ሲሰራ የነበረውን ስራ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚደራጅ የጠቅላይ
ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ፕሬስ ሰክሬታሪው ለሕዝብመ ሆነ ለመገናኛ ብዙሃን ተገቢውን መረጃ ግዜውን
በጠበቀ መልኩ እንዲደርስ የሚያስችል አሰራርን ይከተላል፡፡ ፕሬስ ሴክሬታሪው የመንግስት ቃል አቀባይ በመሆን የሚሰራ ሲሆን የሌሎች
አገራትን ተሞክሮ በመውሰድ የሚደራጅ ይሆናል፡፡ ከመገነኛ ብዙሃ ጋር የሚኖረውም ግንኙነት ቅርበት ያለውና መደበኛ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን
የፕላንና ልማት ኮሚሽን
አሁን ብሔራዊ የልማት ኮሚሽን ተብሎ የሚጠራው የፕላንና ልማት ኮሚሽን
ተብሎ የስም ማስተካከያ የተደረገበት ሲሆን ከዚህ ቀደም በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ይዞ ይቀጥላል። በፖሊሲ ጥናትና ምርምርማዕከል እናበኢትዮጵያ
ልማት ምርምር ኢንስቲቲዩት የሚዘጋጁት የፖሊሲ ጥናቶች ለአገራዊ ዕቅድ ዝግጅት አስፈላጊ ከመሆናቸው
አንጻር በአንድ ላይ “የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት” በሚል ተዋህደው
ለፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ እንዲሆኑ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ ታምኖበታል። በመሆኑም ሁለቱ ተቋማት
ተዋህደው ተጠሪነታቸው
ለፕላንና ልማት ኮሚሽን እንዲሆን ቀርቧል።

4. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትኮሚሽን
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል። የኢንዱስትሪ
ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች
አገልግሎት ድርጅትን በመጠቀለልየኮርፖሬሽኑ ተጠሪነት ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
ይሆናል። ከዚህ
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የመሬት ባንክ ልማትና ኮርፖሬሽን ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ይሆናል፡፡

ሌላው የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸርና ግብርና ኢንቨስትመንት ባለስልጣን በዚህ
አዋጅ የፈረሰ ሲሆን ኢንቨስትመንት ምልመላና ሌሎች በኢንቨስትመንት አዋጅ የተቀመጡ ስልጣንና ተግባራት በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሚሰሩ ይሆናሉ፡፡

8) የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በተመለከተ
የመንግሥት የልማት ተቋማትንበተመለከተ
ከፍተኛ የሆነ የሪፎርም ሥራ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ነው። የሪፎርም ሥራውበዋነኛነት የመንግሥትየባለቤትነት
ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት፤ የልማት ድርጅቶች ተጠሪነት ምን መምሰል እንዳለበት፤ የመንግሥት የቁጥጥርና የባለቤትነት ሚና በአግባቡ
መለየት፤ የቦርድ አሰያየም እና የቦርድ ሃላፊነትን የተሻሉ ልምዶችን በመቀመር እንዲወስን ማድረግ፤ በፕራይቬታይዜሽን የሚተላለፉ
ድርጅቶችን መለየት፤ በመንግሥት እና በግል ዘርፍ የሚኖረው የጆይንት ቬንቸርን ምን መልክ ሊኖረው እንደሚችል፤ እና ሌሎች ጉዳዮች
በዚህ ጥልቅ የሪፎርም ሥራ የሚታይ ሲሆን፤ በአዋጁ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የሚከታተል ኤጁንሲ የተቋቋመ ሲሆን ዝርዝር
ስልጣንና ተግባሩ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል።

[1]እነዚህ ማሻሻያዎች በ2008 ዓ.ም የፍትሕ ሚኒስቴር በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተተካበት፤ በ2010 ዓ.ም ደግሞ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት እና የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት እንዲዋሃዱ
የተደረገበት ነው፡፡
የተደረገበት ነው፡፡
Comments
Post a Comment