በመንዝ ወረዳ ያአቆብ ልብነ ድንግል የነበረበትና ልጆች የወለደበት አገር በባላገሩ በመንዝ ሕዝብ አፍ ምንም
ሲነገር፣ ሲተረክ አይሰማም። አንዲያውም ያአቆብ የሚባል የንጉሥ ልጅ በመንዝ ወረዳ አንደነበረ የሚተርክ አንድ ባላገር
አይገኝም። ያአቆብ የሚባል የንጉሥ ልጅ ልጆች አንደወለደ ወይም በዚህ ጊዜ፣ በዚህ ዘመን ነበረ፣ በዚህ ጊዜ፣ በዚህ ዘመን
ሞተ ማለትን አስካሁን የሰማ የመንዝ ባላገር ወይም ካህን አላገኘሁም። ስግው ቃልና ገራም ፋሲል ስለሚባለው ግን ገፈገፍ
በሚባል ወረዳ፣ አደት ማርያም ገዳም ውስጥ መምሬ አጉኔ የሚባሉ ቄስ ካመጡልኝ ከአርጋኖ መፅሐፍ ዳር የተገኘ
የትውልድ ቁጥር አንዲህ ይላል።
አፄ ንብለ ድንግል ወለደ ለገላውደዎስ፣ ገላውዴዎስ ወለደ ለሰርፀ ድንግል፣ ሰርፀ ድንግል ወለደ ለያአቆብ ይልና
ይጨርሳል። እንደገና ቀጥሎ ካልአ ያአቆብ ወለደ ለፋሲል፣ ፋሲል ወለደ ለሱስንዩስ፣ ሱስንዩስ ወለደ ለፋሲል፣ ፋሲል ወለደ
ለዩሐንስ፣ ዩሐንስ ወለደ ለኢያሱ፣ ኢያሱ ወለደ ለተክለ ሃይማኖት ብሎ ከጨረሰ በቀር ያአቆብ የንብለ ድንግል ልጅ፣ ገራም
ፋሲልና ሥግወ ቃልን ወለደ ብሎ አይናገርም። ደግሞ ገራም ፋሲልና ሥግወ ቃል ያንድ የያአቆብ ልጆች መሆናቸው
አይታወቅም።
ያአቆብ መንዝ ገሜ ላይ ነበረ ስለተባለው በመንዝ ወረዳ ገሜ፣ ገሜ የሚባሉ ሁለት አገሮች አሉ። አንደኛው
በላሎ ምድር ወረዳ አፍቀራ ከሚባለው አምባ ዝቅ ብሎ የሚገኘው የአፈ ንጉስ አጥናፌ አገር ገሜ ማርያም ነው። ሁለተኛው
ደግሞ ግሼ ደጋ ከሚባል አገር የሚገኘው ገሜ ግዩርጊስ የሚባል አረህና ጉራጉር የበዛበት ጥንታዊ ቦታ ነው። ገሜ ማርያም
ከሚባለው ከአፈ ንጉስ አጥናፌ አገር ያአቆብ የንብለ ድንግል ልጅ የሚባል ስሙ ዝክረ ነገሩ የለም። ማንም ሰው ቢጠየቅ
ከቄስ ወይም ከባላገር አንድ ቃል ስለእርሱ የሚተርክ አላገኘሁም። የአገሩ አቅኝም ጌራ ነበር። ርስ የሚባል አማቹ አታሎ
በሸፍጥ ወሰደበት እያሉ ከመፎለል በቀር ስለ ያአቆብ ንብለ ድንግል አንዳች ነገር አያዉቁም። ያእቆብ ፋሲልን ብቻ ወለደ
የሚል የትውልድ ቁጥር አለ።

ይሁን አንጂ ያእቆብንና ሥግው ቃልን አንድነት አድርጎ አወላለዳቸውንም አይናገርም። ከሥግወ ቃል በኃላ ያለውን ትውልድ ከያእቆብ ተያይዞ ወረደ ቃል ሰንበልት የሚል ትውልድ መቁጠር አንዲያውም በፍፁም አይታወቅም። ወይዘሮ ሰንበልት ጥርጥር አልቦ የራስ ፋሪስ ልጅ ናት ብሎ ለመተረክ በላሎ ምድር፣ በአራድማ፣ በአንግዎ፣ በማማ ምድር ያለ ባላገር ሆነ ቄስ፣ ካህን፣ ገበሬ በቃልም በመፅሀፍም አየተመኩ ይተርካሉ። ግን ወረደ ቃል ሰንበልትን ወለደ የሚል ከመጀመሪያ አስከ መጨረሻ አይገኝም። ከቶውንም ወረደ ቃል የሚባል የትውልድ ቁጥር በአንድ ስፍራ ሲተረክ አይሰማም። ሰንብልትንም የወረደ ቃል ወይም የሥግው ቃል ልጅ ናት ብሎ የሚተርክና የሚያምን ሰው የለም። አንድ ሰው እንኩዋ አላገኘሁም። ወይዘሮ ሐመልማልን የወገገደ ሕርያቆስ ልጅ ናት ወይም የጎጃም ሴት ናት ብሎ የሚተርክ ሰው የለም። ግን አንድ ሥፍራ አፄ ፋሲል ከአትዬ ሐመልማል አፄ ሱስንዩስን ወለዱ፣ አፄ ሱስንዩስ ከተጌ ወልደ ሰዓላ ገራም ፋሲልን ወለዱ ብሎ አዘውትሮ የሚተርክ ፅሁፍ አግኝቻለሁ። መንዝ በሚባለው ክፍል ሁሉ የራሱን ትውልድ፣ የራሱን አባት አየቆጠረ ራሱን ከማግነን በቀር የበተመንግስቱን ትውልድ አንስቶ መናገር አይሻም። ቢጠይቁትም የኛ ወገን አይደለም። ይህ የመንግስቶቹ ነው ብሎ ይመልሳል አንጂ ሌላ አይናገርም። ቢናገርም የጎንደርን ነጋሲ ሰብስቴን ወለደ፣ ሰብሥቴ አብዬን ከማለት ሌላ ምንም መተረክ አይችልም። የህዝቡ ትውልድ አልፎ አልፎ በቃልም በመጣፍም ሲተረክ፣ ማማ፣ ላሎ፣ ጌራ፣ ርሴ አያለ በሰፊው የሚተረከው የባላገሩ ትውልድ ተፅፎም ተቆጥሮም አይዘለቅም። የጌራም ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ፣ ጎሴን፣ ዘነበወርቅን፣ አገሌን አገሊትን አያለ የሚተርክ ባገሩ ሁሉ ሞልቶዋል። በፅሁፍ የሆነ ጥንታዊ ታሪክ ምንም አላገኘሁም። ግን ዛተ ጦማር ዘተፈነወት፣ አምአግናጥዩስ፣ ኅበ ካህናተ ሸዋ፣ ኅበ መካንንተ ሸዋ የሚል ስለ ሃይማኖት የተፃፈ ታሪክ ግሼ ደጋ ውስጥ ገሜ ግዩርጊስ ከሚባል ገዳም ከገድለ ተክለ ሃይማኖት ዳር በስተመጨረሻው ይገኛል። አርሱም ስለ ሃይማኖት አንጂ ሌላ አይናገርም። ዘመኑንና ጊዜውን አያመለክትም። ምናልባት አግናጥዩስ ያለውን ከጨጌዎች ቁጥር ቢፈለግ ይገኝ ይሆናል። ለፅፈት የማያደርሰኝ ሆኖ ይዤው ሳልመጣ አንጋቻ ወረዳ አቶ ተደነቀ፣ አቶ ወርቁ፣ መምሬ አብተ ማርያም የሚባሉ ሶስት ሰዎች የነጋሴ ክርስቶስ አባት ለብሶ ይባላል ብለው ይተርካሉ። ግን ልብሶን ማን ወለደው ብላቸው አናውቅም ብለው መለሱልኝ። ደግሞ የነጋሲ እናት ሰንበልት የራስ ፋሪስ ልጅ መሆኗን ብቻ ይናገራሉ። ደግሞ ራስ ፋሪስ የጎጃም ዳሞት የደጃች ረዳን ልጅ ወይዘሮ ፋናን አግብቶ ወይዘሮ ሰንበልትንና ወይዘሮ ዓመተ ዋኒስን ወለደ። ወይዘሮ ሰንበልት ነጋሲን ወለደች የሚል አንድ ሰው ብቻ አግኝቻለሁ። አያይዞ የራስ ፋሪስን ትውልድ ይፅፋል። ትውልድ ራስ ፋሪስ። ራስ ሩም ሰገድ ራስ ወሰን ሰገድን፣ ራስ ወሰን ሰገድ መካኖን፣ መካኖ ራስ ቁም ሰገድን፣ ራስ ኩም ሰገድ ራስ ኢሳያስን፣ ራስ ኢሳያስ ራስ ድንብሎናግን፣ ራስ ድንብሎናግ ራስ ፋሪስን፣ ራስ ፋሪስ ሰንበልትን ብሎ ይጨርሳል። ጣልጥ ባለወልድ ወርቁ ከሚባል ባላገር አጅ የተገኘ የትውልድ መፅሐፍ አንዲህ ይላል። ጉም አስጎምጎምን፣ አስጎምጎም ድል አንበሳን፣ ድል አንበሳ ጎሽ አንበሳን፣ ጎሽ አንበሳ ክም አሳፍርን፣ አማሳፍን፣ ልመንን፣ድንጉዜን፣ ብሎልን፣ ይማርን ይወልዳል። ድንጉዜ አመተ ማርያምን፣ አመተ ማርያም አሜሬን አግብታ ጁኔን፣ ጁኔ ምራንን፣ ነጋሲ ስብስቴን ይላል። 2ኛ የራስ ፋሪስ ትውልድ፣ ወይዘሮ ፅጌ፣ ወይዘሮ አፈዋት ወይዘሮ ጥቁሪትን፣ ወይዘሮ ጥቁሪት ዓረብ ሲስኖስን፣ ዓረብ ሲስኖስ ዓረብ ስዳን፣ ዓረብ ሲዳ ራስ ስምዖንን፣ ራስ ስምዖን ራስ ድሉን፣ ራስ ድሉ ራስ ፋርስን፣ ራስ ፋሪስ ሰንበልትን፣ ሰንበልት ብረት ልቡ ዘወልድ ማርያምን። አርሶአም የገዳሙን አገባችና ነጋስን፣ ነጋሲ የበዛ ጣይን አገባና ስብስቴን ወለደ ይላል። 2ኛ የአፄ ንብለ ድንግል ትውልድ፣ ንብለ ድንግል አቤቶ ያአቆብን፣ ወይዘሮ ቅዱሳንን ከአንዲት ሴት ወለዱ። አፄ ገላውድዩስን፣ ወይዘሮ ተወዳድያን ከአንዲት ሴት። አቤቶ ፊቅጦርን፣ ወይዘሮ ወለተ ሐናን ከአንዲት ሴት ወለደ። አቤቶ ያአቆብ ከንግሥተ አዜብ ተጎንደሬዋ አፄ ፋሲልን። አፄ ፋሲል ከእትዬ ሐመልማል አፄ ሱስንዩስን፣ አፄ ሱስንዩስ ከእትዬ ወልደ ሰዓላ ገራም ፋሲልን ወለደ ይላል። ገሜ ጊዩርጊስ በገሜ ጊዩርጊስ የሚተረከው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ግራኝ ሲያሳድዳቸው ልጃቸው አፄ ይስሐቅ መፃህፍቱንና መሣሪያውን ይዞ ገብቶ ነበር። ኅላ ጊዜው ሲያልፍለት ተነስቶ ሄደ ብለው ይጫወታሉ። እንዳሰብነው ሁሉ ይህ ነገር ተዛውሮ ነው አንጅ፣ ንብለ ድንግል የሚለውን ዘርዓ ያዕቆብ፣ ያዕቆብ የሚለውን ይስሐቅ ብለው አስበው ይመስለኛል። ግን ይስሐቅ በገሜ አገር ምን ያህል ዘመን ኖረ ወይስ ስንት ልጆች ወለደ ማለትን ጨርሰው አያስቡም። በገሜ ጊዩርጊስ ብዙ መፃህፍት የይስሐቅን ስም ያነሳሉና ስለዚህ አፄ ይስሐቅ በግራኝ ግዜ ገሜ ገባ
ብለው አምነዋል። ዘርዓ ያዕቆብም ያሉበት ያዕቆብ የንብለ ድንግል ልጅ ማለት ተስቶአቸው ይመስላል። ያዕቆብ የንብለ ድንግል ልጅ በገሜ አገር መግባቱ እርግጥ ሳይሆን አይቀርም። ገሆር የሚባል አገር ግን ባውራጃው፣ በቀበሌው ተፈልጎ ምንም አልተገኘም። ግን ደግሞ በአንጋቻ አጠገብ ግዎል የሚባል ጠፍ አለ። ምናልባት ገሆር የሚባለውን አገር ግዎል ተብሎ ተጠርቶ በጊዜ ርዝማት ይህን መስሎ ቀርቶ አይታወቅም። ዳግመኛ የነጋሲ ትውልድ እንዲህ የሚባል አለ። ራስ ፋሪስ ያመድ ዋሻ ሳሽን እህት ወስዶ ስንብልትንና ዓመተ ዋኒስን ወለደ። ኅላ ለብሶ የሚባል የሱሪያ ሚካኤል ሰው በነፍስ ግዳይ ከሱሪያ ሚካኤል ተሰዶ ወደ አመድ ዋሻ መስቀል መጣና ስንበልትን አገባ። ከስንበልትም ነጋሲን፣ ስናን፣ ጥላን ወለደ። ነጋሲ የተወለደው በአመድ ዋሻ መስቀል ነው። ነጋሲ ካደገ በኅላ በአመድ ዋሻ መስቀል አጠገብ ሁለት ቀበሌዎች አቅንቶ አንዱን ለስና፣ ሁለተኛውን ለጥላ ሰጠና እርሱ ወደ አንጋቻ ተዛወረ ብለው ይተርካሉ። የነጋሲ ክርስቶስን መንግስት በራስ ፋሪስ በኩል እንደሆነ አንጆ ከንብለ ድንግል ዘር መሆኑን በመንዝ አውራጃ አንድ ሰው የሚያውቅና የሚተርክ እስካሁን አላገኘሁም። የነጋሲ ቅድመአያት ወይም አያት ሥግው ቃል ነው የሚል ደሞ አይገኝም። አንድ የራስ ወልዴ ፀሐፊ አለቃ ተሰማ የሚባል ሰው እንዲህ አለ። ሥግው ቃል የሚል ትውልድ በቀያ፣ በዶባ በኩል የነደጀች ወልደ ሚካኤል ዘር ነው እንጂ የነጋሲ ዘር መሆኑን አናውቅም። ይህን የሚቆጥር የትውልድ መፅሐፍ በራስ ወልዴ እጅ አለ። አንዱንም እኔ ቀብሬዋለሁ፣ አንደኛውንም የራስ ወልዴ የልጅ ልጅ ፊታውራሪ ዘውዴ ይዞታልና በእርሱ እጅ ይገኛል ብለዋል። በአንተ ዘንድ ያለውን መፅሐፍ አሳየኝ ብለውም እኔ ግዝት ነኝ ብሎ ከለከለኝ። ሰውየው ቢፈለግ ግን አገሩ ከዚህ ከገሜ ጊዩርጊስ አጠገብ ነው። ስሙም አለቃ ተሰማ ይባላል። አቶ ፈቄ ከሚባሉ ከገሜ ግዩርጊስ ሹም ዘንድ ለጉዳይ መጥቶ አግኝቼ ጠይቄዋለሁ። ቢፈለግም በቅርብ ይገኛል ወይም ፊታውራሪ ዘውዴ መሸሻ የሚባለውን ማስጠየቅ ይቻላል

Comments
Post a Comment